Get Mystery Box with random crypto!

ኢብራሂምም አለ... رَبِّ هَبْ لِي مِنَ الصَّالِحِينَ ጌታዬ ሆይ! ከመልካሞቹ | Abu_Oubeida~channel

ኢብራሂምም አለ...

رَبِّ هَبْ لِي مِنَ الصَّالِحِينَ
ጌታዬ ሆይ! ከመልካሞቹ የሆነን (ልጅ) ስጠኝ፡፡(37;100)

فَبَشَّرْنَاهُ بِغُلَامٍ حَلِيمٍ
ታጋሽ በሆነ ወጣት ልጅም አበሰርነው፡፡(37;101)

فَلَمَّا بَلَغَ مَعَهُ السَّعْيَ قَالَ يَا بُنَيَّ إِنِّي أَرَىٰ فِي الْمَنَامِ أَنِّي أَذْبَحُكَ فَانظُرْ مَاذَا تَرَىٰ ۚ قَالَ يَا أَبَتِ افْعَلْ مَا تُؤْمَرُ ۖ سَتَجِدُنِي إِن شَاءَ اللَّهُ مِنَ الصَّابِرِينَ

ከእርሱ ጋርም ለሥራ በደረሰ ጊዜ «ልጄ ሆይ! እኔ በሕልሜ እኔ የማርድህ ሆኜ አያለሁ፡፡ ተመልከትም፤ ምን ታያለህ?» አለው፡፡ «አባቴ ሆይ! የታዘዝከውን ሥራ፡፡ አላህ ቢሻ ከታጋሾቹ ሆኜ ታገኘኛለህ» አለ፡፡(37;102)

فَلَمَّا أَسْلَمَا وَتَلَّهُ لِلْجَبِينِ

ሁለቱም ትዕዛዙን በተቀበሉና በግንባሩም ጎን ላይ በጣለው ጊዜ (የሆነው ሆነ)፡፡(37;103)


وَنَادَيْنَاهُ أَن يَا إِبْرَاهِيمُ

ጠራነውም፤ (አልነው) «ኢብራሂም ሆይ!(37;104)

قَدْ صَدَّقْتَ الرُّؤْيَا ۚ إِنَّا كَذَٰلِكَ نَجْزِي الْمُحْسِنِينَ

ራእይቱን በእውነት አረጋገጥክ፡፡» እኛ እንደዚሁ መልካም ሠሪዎችን እንመነዳለን፡፡(37;105)

إِنَّ هَٰذَا لَهُوَ الْبَلَاءُ الْمُبِينُ

ይህ እርሱ በእውነት ግልጽ ፈተና ነው፡፡(37;106)

وَفَدَيْنَاهُ بِذِبْحٍ عَظِيمٍ

በታላቅ ዕርድም (መስዋዕት) ተቤዠነው፡፡(37;107)

وَتَرَكْنَا عَلَيْهِ فِي الْآخِرِينَ

በእርሱም ላይ በኋለኞቹ ሕዝቦች ውስጥ መልካም ዝናን አስቀረንለት፡፡(37;108)

سَلَامٌ عَلَىٰ إِبْرَاهِيمَ

ሰላም በኢብራሂም ላይ ይሁን፡፡(37;109)


Abu fewzan

https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=2949783871948602&id=100007510531167&sfnsn=mo