Get Mystery Box with random crypto!

ማነው አቋም የቀየረው? እስኪ አስተዋይ የሆናችሁ በመረጃ ፍረዱ? አላዋቂዎችን በባዶ ፕሮፖ ገ | Abu_Oubeida~channel

ማነው አቋም የቀየረው?
እስኪ አስተዋይ የሆናችሁ በመረጃ ፍረዱ?

አላዋቂዎችን በባዶ ፕሮፖ ገንዳ የሰለፊይ ኡስታዞቻችንን አቋም ቀይረዋል በማለት ማምታት ከያዛችሁና ንፁሀን ኡስታዞቻችንን ሙመይዕ ሁነዋል እያለችሁ መጮህ ከጀመራችሁ ወራቶችን አስቆጠራችሁ።

ግን እስኪ ከመረጃ አንፃር የትኛውን አቋም ነው የቀየሩት?
በቃ በሁኑ አካላቶች ላይ የሆነ ፍርድ ስፈርዱ ስላልተቀበሏችሁ ብቻ እንድህ ንፁሀንን በለሉበት ስወቅሱ ትንሽ አይሰቀጥጣችሁም እንኳ!?

ለምሳሌ በጣም በሰፊው የምታራግቡት የጀርህ ወተዕዲልን መስአላ የጅቲሀድ መስአላ ነው ብለዋልነው።
እሺ እሄን አቋም አድስ የያዙት አቋም ነው ወይንስ በፊትም ከነርሱው ጋር በነበራችሁበትም ጊዜ እንድሁ ነበር አቋማቸው በመረጃ እንይ ተከተሉኝ:-

አቋማቸውን ቀይረዋል እያሉ ከሚወቅሷቸው ኡስታዞች አንዱ ኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር ነው። እውን ኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር ጀርሕ ወተዕዲልን የጅቲሃድ መስአላ ነው የሚለውን አቋም አድስ ነው የያዘውን?
ልብ በሉ አቋም ቀይሯል ማለት ድሮ "ጀርሕ ወተዕዲል እጅቲሃድን የሚያስተናግድ መስአላ አይደለም ብሎ ዛሬ ደግሞ ነው ቢል" ነበር አቋም ቀይሯል የሚባለው ። እውን በፊት አቋሙ ሌላ ዛሬ ሌላ ነውን? ? ከዚህ በስተፊት ከፃፋቸው መፀሐፍ እና ፅሁፎቹ እስኪ በመረጃ እንመልከት

በ2008 ዓ ል "አልበያነን ጀምዒያ ሱሪና የተብዲዕ ህግጋት" በማለት ያዘጋጀውን መፀሐፍ
ምዕራፍ ሶስት ውስጥ (( "ሙብተዲዕን ሙብተዲዕ ያላለ ሙብተዲዕ ነው" የሚል ኢልዛም አደጋ ሊያስከትል ይችላል)) የሚለውን ንዑስ ክፍል ከገፅ (200–208) በደንብ አንብቡት ያዛኔም ከአምስት አመት በስተፊት አቋሙ ምን እደነበር በግልፅ ታያላችሁ ማን አቋምም እንደቀየረ ታረጋግጣላችሁ። ሰዎቹ ያለምንም መረጃ ንፁሃንን በሌሎበት እየወነጀሉ መሆናቸውን ትታዘባላችሁ!!!
የተወሰኑትን የመፀሐፉን ገፆች በዚህ ሊንክ እየገባችሁ ማንበብ ትችላላችሁ:-
╭─┅──•••••─═ঊঊঈ═─•••••──┅─╮
t.me/IbnuMuhammedzeyn/1073
t.me/IbnuMuhammedzeyn/1074
t.me/IbnuMuhammedzeyn/1075
t.me/IbnuMuhammedzeyn/1076
t.me/IbnuMuhammedzeyn/1077
t.me/IbnuMuhammedzeyn/1078
╰─┅──•••••─═ঊঊঈ═─••••••──┅─╯

በዚሁ መፀሐፍ ገጽ 203 ላይ በግልፅ የጀርሕ ወተዕዲል መስኣላ የጅቲሃድ መስአላ እንደሆነ በግልፅ አማረኛ በማያሻማ ገለፃ እንዲህ ሲል አስቀምጧል «የሂስና የሙገሳ ዘርፍ በራሱ የኢጅቲሃድ ርእስ መሆኑ ሊዘነጋ አይገባም።»
በዚህ ገብታችሁ አንብቡት {{ https://t.me/IbnuMuhammedzeyn/1078 }}
ታዲያ የዛኔ እሄን ካለ ዛሬ አቋም ቀይሯል ማለቱን ምን አመጣው? ውሸት አይሆንባችሁምን? አላህን አትፈሩምን??

እንድሁም (ሴኔ 10/2008 ወንድማዊ ምክር) በሚል ርእስ የፃፈው ጠቃሚ ምክር ላይም እንድሁ አንዱ ሌላውን በተብዲዕ መስአላ ሊያስገድድ እንደማይገባም አካቱ ፅፏል እዚያው ፅሁፉ ላይ እንድህ ይላል «ትላንት ሰለፎቻችን፣ ዛሬም ታላላቅ ዑለማዎቻችን አንዳቸው በቢድዐ የፈረጁትን አካል ሌላቸው ሲከላከሉለት ያጋጥማል፡፡ ግና “እንዴት እኔን ተከትለህ አልፈረጅክም” ብለው አንዳቸው በሌላው ላይ አልዘመቱም፡፡» ሙሉውን የፈለገ በዚህ ሊንክ ገብቶ ማንበብ ይችላል
{{ https://t.me/IbnuMunewor/93 }}
የት ነው የተቀየረው አቋም ድሮም ሆነ ዛሬ በዚህ ርእስ ላይ አቋሙ አንድ ነው።

እንድሁም ኡስታዝ ኸድር አሕመድም ከዚህ በስተፊት ቀደም ሲል በሐጁሪ አንጃዎች ላይ ረድ ሲያደርግ በዚህ መስአላ ላይ ኢልዛም ማድረግ እንደማይገባ የኢልዛምን ቢድዐ የጀመረው ሐጁሪ እንደሆነ ከዘመኑ ዑለሞች እያጣቀሰ በደንብ አስተምሯል።
___
ከዚህ በላይ የጠቀስኳቸው ሐቅ ለሚፈልግ ሰው ማን አቋም እንደቀየረ ማን በድሮው አቋሞ ላይ እንዳለ በመረጃ ግልፅ ያደርጋሉ።

ለራሳችሁ አቋም ቀይራችሁ ንፁሃን ኡስታዞችን ኡማውን የዲኑን ጉዳይ እንዳያስተምሩ አቋም ቀይራችሗል እያላችሁ መወንጀል አግባብ አይደለም።

ካወራችሁ ላይቀር ማውራት ያለባችሁ አቋም ቀይረናል እኛ የስከዛሬው አቋማችን ትክክል አልነበረም ጥፋት ላይ ነበርን ከስከዛሬው አቋማችን ወደ አላህ እንመለሳለን እናንተም እንደኛው ከስከዛሬው አቋማችሁ ወደ አላህ ተመለሱ ነበር ማለት ያለባችሁ። "ጀራፍ እራሱ ገርፎ እራሱ ይጮሃል" አሉ እራሳችሁ አቋም ቀይራችሁ እራሳችሁ አቋም ቀየሩ ብላችሁ ትጮሃላችሁ። ግን ለምን በራሳችሁ ጊዜ አስተዋዬች በአቅላችሁ ላይ እንዲስቁ ትፈቅዳላችሁ።

ለምን በሌለ ችግር ኺላፍ እየፈጠራችሁ የሰለፊያ ደዕዋ በሀገራችን ማደግ ባለበት ደረጃ እንዳያድግ እንቅፋት ትሆናላችሁ?

ወንድማችሁ ኢብኑ ሙሐመድዘይን
​•┈┈•┈┈•⊰✿◇✿⊱•┈┈•┈┈•
t.me/IbnuMuhammedzeyn
t.me/IbnuMuhammedzeyn