Get Mystery Box with random crypto!

አስደሳች ዜና ለሰለፍዮቸ በሙሉ السلام عليكم ورحمة الله وبركاته ውድ እና የተ | Abu_Oubeida~channel

አስደሳች ዜና ለሰለፍዮቸ በሙሉ
السلام عليكم ورحمة الله وبركاته

ውድ እና የተከበራችሁ የመስጂዴ አስሱና ግሩፕ አባላት በሙሉ በያላችሁበት እንዴት ናችሁ?
መቼም አላማችን ላይ ለመድረስ (መስጂዴ ሱና ለመገንባት) ያለንን ጉጉት አሁን እያደረግን ያለው ተሳትፎ ትልቅ ምስክር ነው። ይህ በዚህ ላይ እያለ ከአሱና መስጂድ ግንባታ ጋር ተያይዞ አንድ ወንድማችን ከአሁን በፊት በንያ በነበረው የንያ ፕሮግራም ላይ 4000 ወዴ አካውንት ገቢ አድርጓል። ባለፈው በመስጂዴ ሱና ዙሪያ እየተወያየን ቆይተን ከአሱና መስጂድ ግንባታ ጋር ተያይዞ አንድ ሀሳብ መጥቶልናል። ይህም ምንድን ነው አንድ ወንድማችን ጋር በዛ ያለ ቁጥር ያለው ሪሳላህ አየንና ለምን ለመስጂዴ አሱና ድጋፍ ማድረጊያ አንጠቀመውም የሚል ሀሳብ ስናማክረው እሱም ምንም ሳያወላውል ፈቃደኝነቱን ገልፆልናል። ። ይኸውም ምንድን ነው፤ 5000 ፍሬ እና ከዚያ በላይ የሚሆን አጭር የሪሳላ ኪታብ አለው። አሁን ላይ በችርቻሮ እየሸጠ ያለው አንድ ፍሬ ሰላሳ አምስት(35) ብር ነው። ስለዚህ እርሱ ለመስጂዴ ሱና በ25 ብር እንደሚሸጥልን አስረግጦ ነግሮናል። እኛ ደግሞ ማንኛውም ኪታብ ቤት በሚሸጥበት ዋጋ 35 ብር ልንሸጥ ተስማምተናል። ይህ ማለት በትንሹ ከአንዱ አስር (10) ብር እንኳን ብናተርፍ ከአምስት ሺህ ኪታብ 50,000 ብር ለመስጂዴ አሱና ገቢ ማስገኘት ይችላል። ስለዚህ ማንኛውም አባል በ35 ብር ገዝቶ አሱና መስጂድን እንድረዳ ጥሪ እናቀርባለን።

ማሳሰቢያ፡
ከእንድ በላይ ለቤተሰብም መግዛት ይቻላል፤ ይበረታታልም። ገዝቶ በስጦታ ማበርከትም ይቻላል። ውድ፣የማያልቅ ፣(የማያሩግ) ከትውልድ ወዴ ትውልድ የሚተላለፍ ስጦታ፤
ከኢትዮጵያ ውጭ ላላችሁ ደግሞ የቅርብ ሰው በመላክና ማስገዛት ይችላሉ። በስማቸው አስመዝግበው በአደራ መልክ ካዘዙንም እናደርሳለን፤ እናስቀምጣለንም። አድስ አበባ እና ሌሎች የክልል ከተሞች ወኪሎችን ለማስቀመጥ እንሞክራለን።
የህትመት ችግር ያለበት እንዳይሸጥ ጥረት እናደርጋለን። ባጋጣሚ ቢከሰት ከሶስት ቀን ካልበለጠና ብዕር ካልነካው ለመመለስ ዋስትናውን እንወስዳለን

ኪታቡ ኦሪጅናል ሲሆን ወረቀቱ ክሬም ነው።
ጥቂት ስለኪታቡ፡
የኪታቡ ስም፡ ሙንከራቱን ሻኢአህ ፊልሙጅተመአቲ የጂቡል ሀዘሩ ሚንሀ
منكرات شائعة في المجتمعات يجيب الحذر منها
ጥንቅር፡ አሸይኽ ሙሀመድ ኢብኑ ሂዛም አል በእዳኒይል የመኒይ ሀፊዘሁሏሁ ወረአሁ።
إعداد: الشيخ محمد بن علي بن حزام الفضلي البعداني حفظه الله ورعاه
صاحب فتح العلام بشرح ودراست بلوغ المرام
ሸኽዮውን ፈትሁል አላምን ያወቀ ያውቃቸዋል። ሸይኹ ሰለፍያን እያስተማሩ ያሉ ቆፍጠን ያሉ ሰለፊይ ናቸው አሏህ ይጠብቃቸው እድሜያቸውንም። ያርዝመው።
የኪታቧ የገፅ ብዛት :—64
ወረቀት አይነት: — ክሬም

ኪታቡ እምቅና በጣም ቆንጆ ሲሆን ሁሉን አቀፍ ሆኖ የተወው ርእስ የለም።
ሰላሳ ክፍሎች ያሉት ሲሆን
ከአፀያፊው ሽርክ እስከ ጫት፣ ከድሞ ክራሲ እስከ ፎቶ፣ ከኢኽቲላጥ እስከ ጉቦ እና ሌሎችም በጣም ወሳኝና አንገብጋቢ የሆኑ ርዕሶችን አካታለች።ስለዚህ ባጭሩ ኪሳችን ሳይጎዳ አሱናን በዚህ መልኩ ረድተን የኪታብም ባለቤት እናሆናለን ለማለት ነው። እዚህ ጋር ሁለት ነው አጅሩ ከሌላው ይለያል። አንድም በቀራንበትና ለሌላም ከሰጠነው በቀራበት፤ሌላኛው ደግሞ ለመስጅዱ በረዳንበት።
ለተጨማሪ መረጃ ደሴ ያሉትን አድሚኖች ማናገር ይችላሉ።
መገኛ :— መክተበቱ አሱና ዴሴ


https://t.me/mesjidesunnahbedessie8800
https://t.me/mesjidesunnahbedessie8800