Get Mystery Box with random crypto!

በፍቅር ተይዤ ... ገና በለጋ እድሜዬ ታስሬ በፍቅር ውዴታው አክንፎኝ እየዋለ ሲያድር በወጣት | Abu_Oubeida~channel

በፍቅር ተይዤ ...

ገና በለጋ እድሜዬ ታስሬ በፍቅር
ውዴታው አክንፎኝ እየዋለ ሲያድር
በወጣትነቴ ባልተገብረውም የእምነት ፍቅር ይዞኝ፡
የተውሒዲ የሱና ዲፍረቱ አሥተክዞኝ፡
በሀሣብ በሒሣብ ልረዳው እምነቴን ፡
ለእሥልምናየ ሥል ልሰጠው ማንነቴን፡
እያልኩኝ ሥፅናና ብቻየን በልቤ፡
ከጀግና ሰለፎች አደራን ከትቤ፡
ለምን ይሆን ታዲያ ምኞቴ እማይሰምረው፡
የልፋቴን ውጤት የማላጣጥመው!:
ለምን!?

አቡ ዘከርያ (የህያ ቢን ሙሐመድ አል ዓንበርይ) እንዲህ ይላል፦

" እውቀት ያለ ስርዓት፥ ማገዶ እንደሌለው እሳት ነው፡፡ ስርዓት ደግሞ ያለ እውቀት፥ ነፍስ እንደሌለው ሰውነት ነው፡፡"

[ጃሚዕ አኽላቅ አርራዊ ወአዳብ አስ ሳሚዕ 122/1].

قال الإمام أحمد رحمه الله تعالى:-
"العـلم لا يـعـدله شـيء لمن صحّـت نيـتـه
«ንያውን ላሳመረ ሰው ዕውቀትን መፈለግን የሚያህል ነገር የለም»
قالوا: وكيف تصح نيتـه؟
ሰዎችም እንዲህ ሲሉ ጠየቌቸው እንዴት ነው ንያ ሊያምር የሚችለው ?
قال: ينـوي أن يرفع الجهل عن نفسه وعن غيره"
እርሳቸውም እንዲህ ሲሉ መለሱ ፦ «መሀይምነትን ከራሱና ከሌሎች ላይ ለማስወገድ መነየቱ ነዉ»
=-------------
t.me/sefinetunuh