Get Mystery Box with random crypto!

2ኛ ሚስት! ___ 2ኛ ሚስት መደራረቡ ለጀብድ አይደልም።ደረሳውም ሆነ ገበሬው ስለ ሁለተኛ ሚስት | Abu_Oubeida~channel

2ኛ ሚስት!
___
2ኛ ሚስት መደራረቡ ለጀብድ አይደልም።ደረሳውም ሆነ ገበሬው ስለ ሁለተኛ ሚስት ማሰብ ጀምሯል።የወንድ ወንድ እየተሰማው ነው። የመጀመሪያዋ ሚስቱ ጋር ሲጋጭ በሁለተኛ ሚስት ነው የሚያስፈራራት።
ሁለተኛ ሚስት ማግባት ማለት ለጀብድ የሚፈጸም ሳይሆን ሸሪዓዊ ህግን ተከትሎ የሚደረግ ነው።
አንድቷን በስርኣት ማስተዳደር ሳይችል ሁለተኛ አገባለሁ ብሎ መነሳት:የሸሪዓ መርህን ከመጣስም አልፎ በእህቶች እንባ መራጨትም ነው። አላህን ፍራ"!
እቤት ያለችው ሚስትህ ኑሮየን ብላ እንጂ ደልቷት አይደልም እየኖረች ያለችው። አላህ የበዳዮችን ዱዓ ተቀባይ ነው። የሚለው "ስትበደል"ብቻ አይሁን ትዝ የሚልህ "ስትበድል"ም ሊደርስብህ እንደሚችል እያስተዋልክ።


አቡ_ዑበይዳ
https://t.me/AbuOubeida