Get Mystery Box with random crypto!

ፉላን የተባለው እካል የሸይኽ ፉላን ተማሪ ነው!! ~~~ በእርግጥ ይህንን ርዕስ ሳደርግ ሲያዩ ፉላ | Abu_Oubeida~channel

ፉላን የተባለው እካል የሸይኽ ፉላን ተማሪ ነው!!
~~~
በእርግጥ ይህንን ርዕስ ሳደርግ ሲያዩ ፉላንን ነው የፈለክበት የሚል ስሜት ያቃበዘው መነሳቱ አይቀርም።ቢሆንም ለርሱ ስል ብእሬን አልሰብርም።
||
ወደ ተነሳሁለት ርዕስ ገባሁ።ከቀርብ ጊዜ ወደዚህ በተደጋጋሚ እየሰማነው ያለው ነገር ቢኖር ሸይኽ ፉላን እኮ አል_አል'ላመቱ ፉላን ላይ አመታትን ተምሯል።ስለዚህ እርሱ በነ ፉላን ላይ የተናገረው ንግግር ትቀባላለህ አትቀበልም? እነ ሸይኽ ፉላን እኛ ዘንድ ዓዲሎች (ፍትኀኞች) ስለሆኑ የተናገሩት ነገር አሳምኖናል።ይሄንስ አትቀበሉም?። እና መሰለ የሚያሳፍሩ ንግግሮችን ሲደጋግሟቸው እንሰማለን።በነገራችን ላይ እንደዚህ አይነቱ ንግግር አንድም ከተዋጣለት ከሆነ ጃሂል ወይንም የለየለት ከሆነ ጭፍን ተከታይ የመነጨ ነው።ከፊሉ ሰው የሚሸወደው በተፃፈ አረብኛ ፅሁፍ ወይንም ንግግር እንጂ ከውስጡ ባለው መልእክት አይደለም የሚለካው።ምን ያድርግ የሚችለው ማንበብ እንጂ መረዳት አይደለ'ማ!።ሌላ'ኛው ገና ከወድሁ ሸይኽ ፉላን እኮ ከ አል'ላመቱ ፉላን ላይ ነው የተማረው ሲሉት ፡የተማረባቸውን ሸይኽ ስለሚያከብራቸው ገና ከወድሁ ሳያጣራ የነርሱ ተማሪ ነው ስለተባለ ብቻ መርሃባ ብሎ ይቀበላል።አንድ ሰው የቱን ያክል የላቀ እና የከበረ ሸይኽ ላይ በመማሩ ብቻ የሐቅ ሚዛን ሊሆን አይችልመ።የትልቅ ሰው ተማሪ ስለሆነ ብቻ ጥፋት ካለበት ከጥፋቱ አይቀድሰውም።በዚህ የሚመዝን ካለ እውነትም የወጣለት ጃሂል ነው።ስንቶች በሱሃቦች እጅ ላይ የተማሩ መጨረሻቸው ተበላሽቷል።የመልእክተኛው አለይሂ ሶላቱ ወስ'ሰላም ወሕይ ፀሀፊ የነበረ መጨረሻው ምንድን ነው የሆነው?!ኢማሙ ማሊክ ዘንድ ሲማር የነበረው ደረሳቸው ምንድን ነው የተሐከመበት?! የትልቅ ሰው ልጅ መሆነ ትልቅ አያሰኝም።ውሾች በአንድ ቦታ ተሰባስበው ስለጮሁ ብቻ የግድ ጅብ መጥቷል ማለት አይደለም።(ማንም ቢሆን ተሳድብክ ብሎ እያለከለከ እንዳይመጣ።ምሳሌውን ለምን እንደፃፍኩት የማውቀው ከአላህ በታች እኔ ነኝ)።ተረጋጋና በጥሞና አስተውል እየዘለልክ አትናደፍ።ከዛም ከዚህም አትቅለብለብ።ጉዳው የዲን እንጂ የእልህ ጉዳይ አይደለም።

ሌላኛው፡ ሸይኽ ፉላን በእነ ፉላን ላይ የሰጡት ፍርድ(ሑክም) አሳምኖኛል።ስለዚህ የእነርሱ ፍርድ ያሳምንሃል አያሳምንህም?!የሚል ማስፈራሪያ።አንተን ካሳመነህ ጉዳይህ"!ከዛ ውጪ ያንተ ጭንቅላት ለኔ መሪ ሊሆን አይችልም።እራሱን ችሎ መቆም ያማይችል የቲማቲም አትክልት ሽንብራን መደገፍ አይችልም።ወንበር ላይ ስቀመጥ የምናገረው አላውቅም በሎ በራሱ ለመሰከረ አካል እንዴት ነው በሌሎች ላይ የሚናገረውን የምቀበለው? አንድ ሰው የጀርህ ወአት'ተዕዲል ደረጃ ላይ ይደርስ ዘንድ ቀድሞ ማሟላት ያለበት መስፈርት እንዳለ ከናንተ ሰፈር ስንቶቻችሁ ናችሁ መስፈርቶቹን የምትቆጥሯቸው? ነው ወይስ በዙ የሚጥልባችሁ ነገር ስላለ በሸይኾቻችሁ ላይ ሲሆን ትዘሉታላችሁ? ለነገር መስፈርቶችን ለማስቀመጥ በራሱ ከዛ የትምህርት ዘርፍ የተወሰነ እንኳን ማሽትት ያስፈልጋል።ሀያ"!ተምሪያለሁ የምትለኝ ከሆነ እዛው ከሸይኽኽ ጀምረህ ተግባራዊ እያደረከው ና"?የምትማረው ልትሰራበት አይደል ለመቼህ ነው የምታስቀምጠው?! በነገራችን ላይ የለየላችሁ ጃይሂል ወይንም የወጣላችሁ ጭፍን ተከታይ ስለሆናችሁ እንጂ አንድ ሰው በሐዲስ መዛግብት ደረጃ እንኳን ወደ ቢድዐው ከማይጣራ ከሆነ ሙብተዲዕ እንኳን ሐዲስ ይዘገባል ሲሉ ፡በሌላ በኩል ሱኒ እንኳን ሆኖ ውሸታም ከሆነ ሓዲሱ አይያዝለትም የሚለው ጠፍቷችሁ አይደለም።አይናችሁ ላይ የተሰገሰገው አቧራ አጣርቶ ማየትን ስለነፈጋችሁ እንጂ።ደግሞ የሚዋሽ ሁኖ ሱንይ አናውቅም አትበሉ እንጂ!።
ለአንተ ከማይመጥንህ ቦታ አትግባ ሰላም ትሆናለህ።

የቴሌግራም ቻነል:
https://t.me/AbuOubeida