Get Mystery Box with random crypto!

የሚገርም!! ~~ ሰው የኪታብ ዋጋ ዋጋ አይመስለውም።የእንቁላል ዋጋን ያክል እንኳን ግምት የሚሰጠው | Abu_Oubeida~channel

የሚገርም!!
~~
ሰው የኪታብ ዋጋ ዋጋ አይመስለውም።የእንቁላል ዋጋን ያክል እንኳን ግምት የሚሰጠው አይመስልም።አንዳንድ ሰው ሲዋስህ ዝም ብለህ ሂደህ ከመክተማ በነፃ አንስተህ የምታመጣው ይመስለዋል መሰልኝ።ተውሶ አይመልስም።አንደ ቀልድ ላንብብ ብሎ ወስዶ የውሃ ሽታ አድርጎት ይቀራል።ይሄ ጉዳይ እንደኔ የተሰማው ካለ የብዙ ሰው ሞራል ተጎድቷል ማለት ነው።በጊዜ ርዝመት ምክንያት ለማን እንኳን እንዳዋስክ የረሳኻው ሰው የለም?!በቃ የተዋሳችሁ አካላቶች ይሄ መልእክት ከደረሳችሁ የእስከዛሬው ይበቃል መልሱልን።ባረከሏሁ ፊኩም።

አቡ_ዑበይዳ(ሰዒድ)
https://t.me/AbuOubeida