2022-02-27 20:29:31
የውይይት ጥሪ
~~
1- ለሸይኽ ዐብዱልሐሚድ፣
2- ለሸይኽ ሐሰን ገላው
3- ለኡስታዝ በሕሩ ተካ
4- ለኡስታዝ ዩሱፍ አሕመድ
5- ለወንድም ሑሴን ሙሐመድ አሲልጢ
6- ለወንድም ዐሊ ሑሴን
-----
ከሆነ ጊዜ ጀምሮ የሚራገበው ፊትና ከዛሬ ነገ ከመሻሻል ይልቅ እየባሰበት መሄዱ ለማንም የሚታይ ነው። ጉዳዩ ይበልጥ በተራገበ ቁጥር ብዙ ሰው እየተፈተነ እንደሆነ እያየን ነው። ፊትናው ምንም እንኳ ለጊዜው ብዙ ሰው እየጎዳ ቢሆንም ከማንም በላይ የሚጎዳን ግን እኛኑ እራሳችንን ነው። ምክንያቱም በያንዳንዱ በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ በኛ ሰበብ ከመስመር በሚርቀው፣ ግራ በሚጋባው፣ በደል ላይ በሚሰማራው ሁሉ ከአላህ ፊት ተጠያቂ እንሆናለንና።
ስለዚህ እባካችሁን! በአቋማችሁ እርግጠኝነት ካላችሁ በሰከነ መልኩ ህዝብ እየታዘበን እንወያይ። እንተራረም። ስህተቱ ከኛ ከሆነ በአላህ ስም እምላለሁ ለመመለስ ዝግጁ ነኝ። ሌሎችም ወንድሞች እንዲሁ። እናንተም በዚህ መልኩ እራሳችሁን አዘጋጅታችሁ ቅረቡ።
1- ፈቃደኝነታችሁ ከታወቀ ውይይቱ ጤናማ በሆነ መልኩ እንዲካሄድ የሚያግዙ ነጥቦችን አብረን እናወጣለን።
2- መካተት አለበት የምትሉት ሰው ካለም ይካተታል።
ለምን ባደባባይ ጥሪ ማድረግ አስፈለገ የሚል ሊኖር ይችላል። ምክንያቱ ሁለት ነው፡፡
1ኛ፦ ጉዳዩ ምስጢር ሳይሆን ይልቁንም በሰፊው የሚራገብ ስለሆነ፣
2ኛ፦ ከዚህ በፊት ለብቻ የተደረገው ውይይት ፍሬ አልባ ከመሆኑም በላይ ጭራሽ ነገሮች ይዘታቸው እየተቀየረ ሲናፈሱ ስለነበር ነው።
~
ስለዚህ በግልፅ ተወያይተን ቢቻል እንተራረም። ካልሆነም ሑጃ ለማቆም ይረዳችኋል።
(لیَهۡلِكَ مَنۡ هَلَكَ عَنۢ بَیِّنَةࣲ وَیَحۡیَىٰ مَنۡ حَیَّ عَنۢ بَیِّنَةࣲۗ)
ከኛም ይሁን ከናንተ በተነሳ ሀሰተኛ ዘመቻ፣ አሉባልታ፣ የተሳሳተ ትንታኔ ምክንያት የተሸወደ ካለም ውይይታችንን ተከታትሎ የሚበጀውን ይወስን።
እንደምታውቁት ሶሐባው ኢብኑ ዐባስ ረዲየላሁ ዐንሁ ከኸዋሪጅ ጋር ተወያይተዋል። ከሌሎችም ሰለፎች እንዲሁ ተመሳሳይ ነገር ተገኝቷል። ይህን የምጠቅሰው ለውይይት ተጠርተው "ከሙብተዲዕ ጋር መወያየት አይቻልም" በሚል ማመሀኛ የሸሹ ሰዎች ሁኔታ እንዳይደገም ነው።
ስለዚህ ቢሆንልን እንግባባለን። ካልሆነም የደረስንባቸውን ነጥቦች ሁለታችንም ለምናምንባቸው ዐሊሞች በጋራ ፅፈን እናቀርባለን።
* ይህንን ጥሪ ያነበባችሁ በተለይም ደጋግማችሁ "ብትወያዩ" ስትሉ የነበራችሁ በአድራሻቸው በመደወል ወይም በመላክ ወይም በአካል ቀርቦ በማናገር መልእክታችንን አድርሱልን።
* ለውይይቱ ፈቃደኛ ከሆናችሁ ከስር በቀረበው ሊንክ ግሩፑን እንድትቀላቀሉ እጋብዛለሁ። ሌሎቻችሁ በዚህ ፊትና የተነካኩ ወይም ግራ የተጋቡ፣ ወይም መከታተል የሚፈልጉ ሰዎችን ብቻ አስገቡ። ያገኛችሁትን ሁሉ ዝምብላችሁ add አታድርጉ።
-
https://t.me/+AkvdZdEAY-FiZjM0
241 views17:29